Back to Top
ድግምት እውነታ አለውን? ወይንስ ከእውነታ የራቀና በምናብ ላይ የተቀረፀ ወይም የሚመሳሰል ነገር ብቻ ነውን?

ጥያቄ(41): ድግምት እውነታ አለውን? ወይንስ ከእውነታ የራቀና በምናብ ላይ የተቀረፀ ወይም የሚመሳሰል ነገር ብቻ ነውን?
መልስ:

ድግምት ያለምንም ጥርጥር እውነታ ያለው ነገር ነው። በተጨባጭም ተፅእኖ ያሳድራል። ነገር ግን አንድ ነገር ወደሌላ ነገር መቀየር ማለትም የማይቀሳቀስን ነገር ወደሚንቀሳቀስ አሊያም የሚንቀሳቀስን ነገር ወደ ሰከነ ነገር መቀየር አይችልም ይህ ከእውነታ የራቀ ነገር ነው። ይህ እውነታን የሚመሳሰል ነገር ግን እውነት ያልሆነ ነገር ነው። የፊርዓውን ተከታይ የነበሩትን ደጋሚዎችን አስመልክቶ አላህ ያለውን ተመልከት፦

”(በትሮቻቸውን ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸው፡፡ አስፈራሩዋቸውም፡፡ ትልቅ ድግምትንም አመጡ፡፡” [አልአዕራፍ:116]

ሰዎች ዓይን ላይ እንዴት ሊደግሙ ቻሉ? ሰዎች ዓይን ላይ በትሮችና ገመዶች የሚንቀሳቀሱ ዘንዶች ሆነው ታያቸው። ሱረቱ ጧሃ ላይ አላህ እንዳለው፦

“ወዲያውም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ (እባቦች) ኾነው ወደርሱ ተመለሱ፡፡” [ጧሃ:66]

 ድግምት ነገሮች ወደ ተቃሪኒያቸው መቀያየር ማለትም የሚንቀሳቀስን ወደ ሰከነ ነገር የሰከነውን ወደሚንቀሳቀስ ነገር መለዋወጥ አይችልም። ነገር ግን ዓይኑ ላይ ድግምት የተሰራበት ሰው ነገሮችን በተገላቢጦሽ መመልከቱ ይኸውም የሚንቀሳቀስን የሰከነ ነገር ሆኖ የሰከነው ደሞ የሚንቀሳቀስ ሆኖ እንደሚታየው ለማንም ግልፅ ነው። ይህ ከሆነ አዎን ሀቂቃ አለው ስለሆነም ሲህር የተሰራበት ሰው አካሉ፤ አዕምሮውና ህዋሳቱ ላይ ተፅእኖ አለው ምናልባትም እስከሞት ያደርሳዋል።




Share

ወቅታዊ