Back to Top
ነጃሳዎች ከአይነትና ከምንነት አንፃር ፍርዳቸውን ቢገልፁልን?

ጥያቄ(80): ነጃሳዎች ከአይነትና ከምንነት አንፃር ፍርዳቸውን ቢገልፁልን?
መልስ:

በጠሃራ ቦታ ላይ ነጃሳ በሚወድቅበት ጊዜ ማጠብ እና ቦታውን ማፅዳት በእኛ ላይ ግዴታ ይሆንብናል። ጠሃራ መሆን ያለበት ነገር፣ጠሃራ አደራረጉ እንደ ሁኔታው ይለያያል።

አንደኛው፦ ነጃሳው መሬት ላይ ከሆነ በዓይን የሚታየውን የነጃሳ ክፍል ካስወገድን በኋላ በላዩ  ላይ ውሃ ማፍሰስ ብቻ በቂ ነው። ምክንያቱም  የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አንድ ገጠሬ መስጊድ ገብቶ  ጫፍ ላይ በሸናበት ጊዜ ለሰሃቦቹ ፦ “ተዉት! በባልዲ ውሃ ሽንቱ ላይ ድፉበት።” አሏቸው። ስለዚህም ነጃሳው ምድር ላይ ከሆነ ነጃሳው ጠጣርና በዓይን የሚታይ ከሆነ መጀመሪያ እሱን እናስወግዳለን፤ከዚያም ላዩ ላይ ውሃ አንዴ እናፈስበታለን አበቃ።

ሁለተኛው፤ ነጃሳው ከመሬት ውጭ ባሉ ነገሮች ቢሆን እሱም የውሻ ነጃሳ ቢሆን እንበልና ነጃሳውን ለማጥራት ሰባቴ ማጠብ ግድ ይላል። አንደኛው በአፈር መሆን ይኖርበታል። መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋልና፦ “የውሻ ልጋግ እቃችሁን ቢነካ ሰባቴ  በውሃ ይጠበው አንዱን በአፈር ይጠበው።”

ሦስተኛው፤ ነጃሳው መሬት ላይ ካልሆነ የውሻም ነጃሳ ባይሆን እዚህ  ላይ ሚዛን የሚደፋው አቋም በስንትም ይታጠብ ነጃሳው የሚወገድ ከሆነ ጠሃራው ይገኛል የሚለው ነው። በአንድ ወይም በሁለት ወይም ሦስት አራት ወይም በአምስት ትጥበት ሊሆን ይችላል ነጃሳው የሚወገደው። ዋናው ቁም ነገር በአይን የሚታየው ነጃሳ እስከተወገደ ጠሃራው ይገኛል። ነገር ግን ከወተት ውጭ ሌላ ምግብ ያልተመገበ ህፃን ሽንት አስመልክቶ ሽንቱ የነካውን ቦታ በዛ ያለ ውሃ ማርከፍከፍ በቂ ነው። ማጠብና ማሸት አያስፈልገውም። ምክንያቱም ከወተት ውጭ ሌላ ምግብ ያልተመገበ ህፃን ሽንት ነጃሳው ቀለል ያለ ነው።




Share

ወቅታዊ